• Call Us
  • +25146 2206572

በኤች አይቪ እና በኮሮና ቫይረስ መከላከል መቆጣጠር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ፡፡

 አቶ ማቲዎስ ሞገስ  በደቡብ/ብ/ብ/ህ/ክልል መንግስት በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የኤች አይቪና የኮሮና ቫይረስን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ ላይ በተዘጋጀው መድረክ ለቢሮው ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ፡፡

የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ድይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የቢሮው ሀላፊ ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ትእግስት አበበ እንደገለጽት በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ኋላ እየጎተተ ያለውን የኮሮና ቫይረስና ኤች አይቪን በተመለከተ ከጤና ሚኒስቴር በተሰጠው መመሪያ መሰረት ሀገራዊ ልማትን ለማፋጠንና የተቋማችን አላማ ግቡን እንዲመታ ለማድረግ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣተር የሚያስችሉ ነገሮችን ላይ በጋራ መስራት ይኖርብናል ሲሉ መድረኩ መከፈቱን አብስረዋል፡፡

ስለኮሮና ቫይረስ በሽታ አስመልክቶ ከክልሉ ጤና ቢሮ የመጡት የበሽታውን (የቫይረሱን) መተላለፊያ መንገዶች ከገለጹ በኋላ በሽታው ቀጥተኛ በሆኑና ቀጥተኛ ባልሆኑ መንገዶች ይተላለፋል ብለዋል፡፡ ስለነዚህም መተላለፍያ መንገዶች ዘርዘር አድርገው ከገለጽ በኋላ መንግስትም መመሪያ አውጥቶአል ይህም ከኮቪድ ከተያዙ ከቤት እንዳይወጡ፣ስብሰባና የአደባባይ ሰልፍ እንዳያደርጉ፣ የመመርመር አቅምን መጨመር፣ የክትባት መጠንን ማሳደግ ይህ የውዴታ ግዴታ መሆኑን ግልጸው አለምን እያሳቀቀ ያለውን በሽታ ማስቆም የምንችለው በጋራ በመተጋገዝ መከላከል ስንችል ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ስለኤች አይቪ ቫይረስም ስልጠና የሰጡት አቶ ሀብታሙ ኃ/መስቀል እንዳሉት አሁንም ይህ ቫይረስ ሰዎችን መግደሉን ስላላቆመና ከዚህ በሽታም ፍጹም መዳን ስለማይቻል እኛም ሶስቱ 90ዎች ላይ እስክንደርስ ድረስ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ህብረተሰቡን ማስተማር አለብን በማለት ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ከቢሮው ሰራተኞች ለተነሳው ጥያቄ የሳ/ኢ/ቴ/ቢሮ የኤች አይ ቪ ሜኒስቴሪሚንግ የሆኑት ወ/ሮ አየሁብርሀን ቡቄ ምላሽ ከሰጡ በኋላ መድረኩ ተጠናቆአል፡፡